+251 911 02 84 09
Staff Login
Logo

Gedeo Zone Finance & Plan Department

የጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ

Official Government Portal

የመንግሥት መረጃ ፖርታል

economy

‎በፋይናንስ አሰራር ግልጽነትንና ተጠያቂነትን በመዘርጋት ቀልጣፋ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት ሊሰራ ይገባል ተባለ

August 03, 2026 1 Views
‎በፋይናንስ አሰራር ግልጽነትንና ተጠያቂነትን በመዘርጋት ቀልጣፋ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት ሊሰራ ይገባል ተባለ
‎በፋይናንስ አሰራር ግልጽነትንና ተጠያቂነትን በመዘርጋት ቀልጣፋ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት ሊሰራ ይገባል ተባለ

‎(#ዲላ ሀምሌ 24/2018 ዓ.ም) በፋይናንስ አሰራር ግልጽነትንና ተጠያቂነትን በመዘርጋት ቀልጣፋ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ የጌዴኦ ዞን ፋይናንስ ልማትና ፕላን መምሪያ ገልጸዋል ።

‎የጌዴኦ ዞን ፋይናንስ ልማትና ፕላን መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም እና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ዙሪያ የምክክር መድረክ አካሂዷል ።

‎በመድረኩ የመምሪያው ኃላፊ አቶ ግርማ ጤካሞ፣ የየወረዳውና የከተማ አስተዳደር የፋይናንስ ኃላፊዎች፣ የኦዲት ባለሙያዎችና የዘርፉ ተጠሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

‎በወቅቱ በበጀት ዓመቱ የተመዘገቡ ስኬቶች፣ ያጋጠሙ ውስጣዊና ውጫዊ ተግዳሮቶች እንዲሁም የልማት ፕሮጀክቶች አፈጻጸም በዝርዝር ተዳሰዋል።

‎የጌዴኦ ዞን ፋይናንስ ልማትና ፕላን መምሪያ ኃላፊ አቶ ግርማ ጤካሞ በወቅቱ እንዳሉት የፋይናንስ ሥርዓትን ማጠናከር የዞኑ ልማት መሠረት መሆኑን ጠቁመዋል ።

‎የገቢ አሰባሰብ አቅምንና የበጀት ቁጥጥርን በማሳደግ የዞኑን የልማት ፍላጎቶች ለማሟላት በተደረገው ርብርብ ውጤት መመዝገቡን ገልጸዋል ።

‎በተለይም የመንግስት በጀት አጠቃቀምን ውጤታማ ማድረግ እና የኦዲት ግኝቶችን በፍጥነት ማረም ተቋማዊ ግዴታችን ነው ብለዋል።

‎በመሆኑም ግልጽነትና ተጠያቂነትን ያሰፈነ እንዲሁም ተገልጋዮችን ባከበረ መልኩ የተሳለጠ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል መሆን እንዳለበት አቶ ግርማ አሳስበዋል።

‎አያይዘውም ተግዳሮቶችን በቅንጅት መወጣት በበጀት ዓመቱ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ከውስጥም ከውጭም ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን ለመፍታት ጠንካራ ርብርብ መደረጉንም አብራርተዋል ።

‎በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ በቀጣዩ 2019 በጀት ዓመት የዞኑን ልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ወደ አዲስ ምዕራፍ ማሸጋገር ይኖርብናል ተብሏል።

‎አሰራርን በቴክኖሎጂ ማዘመን የፋይናንስ መረጃዎችን ጥራትና ፍጥነት ለመጠበቅ አሰራሮችን በዘመናዊ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የታገዙ ለማድረግ አቅጣጫ ተቀምጧል ።

‎የፋይናንስ ስርዓትን ማስከበር የበጀት ብክነትን በመከላከልና ህጋዊ አሰራርን በመከተል የህዝብና የመንግስት ሀብት ለታለመለት የልማት አላማ ብቻ እንዲያውል በማድረግና የህዝብ አገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል የህዝቡን መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ የተቀላጠፈና ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል አጠቃቀም እንዲኖር መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል ።

‎የጌዴኦ ዞን ፋይናንስ ልማትና ፕላን መምሪያ ከያዘው ራዕይ አንጻር የፋይናንስ ዲስፕሊን መከበር ለዞኑ ሁለንተናዊ እድገት ወሳኝ በመሆኑ፣ በ2019 በጀት ዓመት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል።

‎በመድረኩ የመምሪያው ሀላፊ አቶ ግርማ ጤካሞ፣ የየወረዳውና የከተማ የፋይናንስ ኃላፊዎች በመገኘት ለቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ የጋራ መግባባት ፈጥሯል ።
Share this article: